የፋይዳ መታወቂያ ሥርዓትን ቀደም ብለው ከተገበሩ ሀገራት መካከል ኢስቶኒያ አንዷ ናት። ጂቢጂ (gbg.com) እንደዘገበው፣ ዜጎች ዲጂታል መታወቂያቸውን በመጠቀም ከ99 በመቶ በላይ የመንግሥት አገልግሎቶችን በኦንላይን ማግኘት ችለዋል። በዚህም “ኢ–አይ–ዲ” (EID) ተብሎ በሚጠራው የኢስቶኒያ ዲጂታል መታወቂያ አማካኝነት የሀገሪቱ ዜጎች ከ600 በላይ አገልግሎቶችን እንደሚያገኙ መረጃው አመልክቷል።

እንደ መረጃው ከሆነ፣ ዜጎች በኦንላይን ምርጫ መሳተፍ፣ የግብር ክፍያ መፈጸም፣ የጤና አገልግሎቶችን በቀላሉ ማግኘት እና የንግድ ፈቃድ ምዝገባ ማድረግ ዲጂታል መታወቂያው ያስገኘላቸው ዋና ዋና አበርክቶች ናቸው። በተጨማሪም ቢሮክራሲን በእጅጉ የሚቀንስ እና ጊዜን የሚቆጥብ ሲሆን፣ ኢስቶኒያውያን በዓመት በአማካይ አምስት የሥራ ቀናት መቆጠብ እንዲችሉ መረጃው ያመለክታል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ ኢትዮጵያም የፋይዳ ብሔራዊ የመታወቂያ አገልግሎትን ባለፈው ዓመት መተግበር ጀምራለች። የአማርኛ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በ2011 ዓ.ም ባሳተመው የአማርኛ መዝገበ ቃላት “ፋይዳ” ለሚለው ቃል ጥቅም፣ እርባና ማለት እንደሆነ አቻ ትርጉሙን አስቀምጧል፤ “ፈየደ” ለሚለው ቃል ደግሞ ጠቀመ፣ ረባ ይላል።

ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባዮሜትሪክና ዲሞግራፊክ መረጃዎችን ከነዋሪዎች በመሰብሰብ አንድን ሰው በልዩ ሁኔታ መለየት የሚያስችል፣ ለሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማንነትን በማረጋገጥ እና በኤሌክትሮኒክ መንገድ ደንበኞቻቸውን ማወቅ የሚያስችል ታማኝነት ያለው የዲጂታል ማንነት ምዝገባ ሥርዓት ነው።
ፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ከሌሎች የሚለይበት

ፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያን ከሌሎች የሚለዩት ባህሪያት አሉት። ለማሳያም፣ አንድ ሰው አንድ መሆኑ የሚረጋገጥበት ሲሆን፣ “የፋይዳ ቁጥር” ተብሎ የሚጠራውን የ12 እስከ 16 አሀዝ (ዲጂት) ያለው መለያ ቁጥር በካርድ፣ በወረቀት ወይም በስልክ በማሳየት አገልግሎት ማግኘት የሚቻልበት ሥርዓት መሆኑ ነው።

ፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ በልዩ የፋይዳ ቁጥሩ ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ጋር በቀላሉ መገናኘት የሚያስችል መሆኑ ዋና ባህሪው ነው።

ለማስተዋወቅና ከክልል ወደ ክልል ለማስተሳሰር ይረዳል። ለምሳሌ፣ በባሕር ዳር ላይ ያለውን ሥርዓት ከአዳማ፣ ከአዋሳ፣ ከመቀሌ እና ከሌሎች ከተሞች ያለው ሥርዓት ጋር የሚያስተሳስር ወጥ የሆነ የግንኙነት መረብ ይፈጥራል።

ግላዊ መረጃን ምስጢራዊ አድርጎ የሚጠብቅ ሲሆን፣ አስተማማኝነቱም ከሌሎች መታወቂያዎች ልዩ ያደርገዋል። እንደ ሀገር የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ ወጥቶ ተግባራዊ መሆኑ ይታወቃል፤ ዲጂታል መታወቂያውም አዋጁን የጠበቀ፣ ያከበረና በዚህ አግባብ የሚመራ ሥርዓት ነው።

ሰዎች ሲመዘገቡ የሰጡት ማስረጃ ባለቤትነቱ የተመዘጋቢው ነው። እያንዳንዱን መረጃ ማየት ሲፈለግም የመታወቂያው ባለቤት ተጠይቆ በፈቃዱ የሚያጋራው እንጂ፣ ባለሙያ ምዝገባውን ካከናወነ በኋላ የተመዘገበውን መረጃ የሚያይበት ሥርዓት አይደለም።

ፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ አራት መርሆች አሉት፤ እነዚህም አካታችነት፣ አስተማማኝነት፣ የተመጠነ መረጃ መውሰድ እና ተናባቢነት ናቸው።

መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ እንዲገነዘቡት እንደ ሀገር ካለው ሕዝብ 40 በመቶው ራሱን የሚገልጽበት ምንም ዓይነት መረጃ ወይም ማስረጃ (መታወቂያ) የለውም። ይህን አሳሳቢ ጉዳይ ግምት ውስጥ በማስገባት የተለያዩ 33 ማስረጃዎችን (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ የመኪና ባለቤትነት ማረጋገጫ /ሊብሬ/፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ…) በማቅረብ መመዝገብ የሚቻልበት ሥርዓት ነው።

ማስረጃ የሌላቸው በአብዛኛው የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ በተለያዩ ማዕከላት የሚኖሩ አቅመ ደካሞች፣ ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሕፃናት ፋይዳ መታወቂያ ያላቸውን ሰዎች ምስክር በማድረግ፣ ባለበት ተቋም ወይም እነዚህን ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ ወይም አገልግሎት ለመስጠት ከተቋቋመ መሥሪያ ቤት ጋር በመናበብ መታወቂያውን የሚያገኙበት ሥርዓት ነው።

ፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያውን በዜግነት ኢትዮጵያዊ ሆነም አልሆነ በሀገሪቱ ነዋሪ እስከሆነ ድረስ የመኖሪያ ወይም የሥራ ፈቃድ በማየት አገልግሎቱ ይፈቀድለታል።

ከዕድሜ አኳያም ከተወለዱ ጀምሮ የምዝገባ ሥርዓቱ ተዘጋጅቷል። ከዜሮ እስከ አምስት ዓመት ያሉ ሕፃናት በሥነ ሕዝብ (ዲሞግራፊ) መረጃ ብቻ የምዝገባ አገልግሎት ያገኛሉ፤ ከአምስት ዓመት በላይ ያሉ ልጆች ደግሞ በሥነ ሕዝብና በአካላዊ መረጃዎች (ባዮሜትሪክ) በመውሰድ ይመዘገባሉ። በአሁኑ ወቅትም በሀገሪቱ ከአምስት ዓመት ጀምሮ ያሉ ሕፃናትን ብቻ ተደራሽ ለማድረግ በትምህርት ቤቶች እና

ከሁሉም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር በ55 ተቋማት አገልግሎቱ እየተሰጠ ነው።
ከአምስት ዓመት ጀምሮ ለሚወለዱ ሕፃናት ብሔራዊ መታወቂያ ለመስጠት መሠረት የሚያደርገው አካላዊ የሆኑ የእጅ፣ የዓይን ብሌን እና የፊት ገጽታ አሻራዎች ናቸው።

ይህም በትምህርት ሥርዓቱ ከማጭበርበር ጋር ተያይዞ ሕፃናት በትክክል ዕድሜያቸው ለአቅመ ሕይወት እና ለአቅመ ሰውነት እስኪደርሱ አገልግሎቱ ወጥ እንዲሆን እና የትምህርት ሥርዓቱን በቁጥር የሚመራ (ዲጂታላይዝድ) ለማድረግ ትልቅ ጠቀሜታ እንዲኖረው ታስቦ ነው።

ልጆች የሀገር ተረካቢዎች እንደመሆናቸው አድገው በትልልቅ ተቋማት ሲያገለግሉ ወይም በትምህርት ላይ እያሉ የውጭ የትምህርት ዕድል ሲያገኙ የስምና የትውልድ ቀን ስህተት እንዳይፈጠር ያግዛል።

በተለያዩ ጊዜያት ሕዝቡን ተጠቃሚና ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል። በዚህ አግባብ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት ዘርፎች የሚከናወኑ ተግባራት በዲጂታል ሥርዓት ካልተደገፉ ስኬታማ የመሆን ዕድላቸው ዝቅተኛ ነው።

ይህንን አገልግሎት በማሳደግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን፣ በየተቋማቱ አገልግሎት ለማግኘት የሚገጥሙ እንግልቶችን እና ምልልሶችን ማስቀረት ይገባል፤ ለዚህም የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ሥርዓት መሠረታዊ ሚና ይጫወታል።

እንደ ሀገር ወደ ዲጂታል ዓለም ለመግባት አራት አስቻይ ነጥቦች ላይ መስራት ይገባል፤ እነሱም ኃይል (መብራት)፣ ዳታ/ኮሙኒኬሽን፣ ዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እና በሀገሪቱ እየተተገበረ ያለው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ናቸው።

ሀገር ካላት ሀብት ዋናው ሕዝብ ነው። በመሆኑም እንደ ሀገር ያለውን ሀብት መመዝገብና ማወቅ አገልግሎት ለመስጠት ያስፈልጋል። የፋይዳ መታወቂያ አንድ ሰው አንድ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሥርዓት በመሆኑ ጥቅሙ እጅግ የጎላ ነው።

የጂዲፒ (GDP) እንደ ሀገር ማግኘትን የሚያስችል ሥርዓት ነው።
የፋይዳ መታወቂያ ማንነትና መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015 ዋና ዋና ገጽታዎቹን በተመለከተ በገጹ እንደተሰፈረው፣ ዘመናዊ የመታወቂያ ሥርዓት በአንድ ሀገር ውስጥ ተግባራዊ ሲደረግ መሠረታዊ ተብለው የሚጠሩ በርካታ ጠቀሜታዎች ይኖሩታል።

ከእነዚህ ጠቀሜታዎች መካከል ሀገራዊ ልማትን በአግባቡ ለማቀድ፣ ምጣኔ ሀብታዊ ሽግግር ለመፍጠር፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ የሀብት ብክነትን ለመቀነስ፣ ወንጀልን ለመከላከል፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹና የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን ለመቅረፍ እና አካታችነትን ለማጎልበት የሚረዳ መሆኑ ተረጋግጧል።

በኢትዮጵያም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የበለፀገ፣ ዘርፍ ተሻጋሪ እና መሠረታዊ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ተቋቁሞ ለአለፉት ሁለት ዓመታት በግንባታና በሙከራ ሂደት ላይ ቆይቷል።

በዚህ ሂደት ውስጥ ከተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ጋር ለማስተሳሰር የሙከራ ትግበራ ሥራዎች ተከናውነው፣ አሁን ነዋሪዎችን መመዝገብና የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ማድረግ መቻሉን መረጃው ያመለክታል።

ምስጢራዊነቱ

የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ የሆኑ አንዳንድ ሰዎች መታወቂያ ካርዱን ለማግኘት ከጊዜና ከእንግልት አንፃር ቀላል ቢሆንም፣ ሲታተም (ኮፒ ሲደረግ) የጀርባው ምስጢር ይገለጣልን? የሚል ስጋት ያነሳሉ።

ይህ ምን ያህል እውነት ነው? ብለን አቶ ኦሊናን ጠይቀናቸው ነበር። አቶ ኦሊና በምላሻቸው ሁለት ቁጥሮች (የፋይዳ 12 እና 16 ዲጂት) እንደሚሰጡ ገልጸው፣ “ተለዋጭ ቁጥር” የሚባለው 16 ዲጂት ያለው ቁጥር መሆኑን ተናግረዋል።

ይህንን ቁጥር ሰዎች አገልግሎት ሲፈልጉ እንዲያጋሩ ይመከራል ብለዋል። የፋይዳ 12 ዲጂት ቁጥሩን ቢያጋሩም ምንም ዓይነት ችግር እንደማይፈጠር አረጋግጠዋል። ለዚህም ተገቢ የደህንነት ጥበቃ አሠራር መኖሩን መረጃዎች ያመለክታሉ።

መታወቂያው በምን መንገድ መያዝ ይገባል?

ምዝገባ ከተካሄደ በኋላ መታወቂያ ይሰጣል፤ ሥርዓቱ ዲጂታል ነው። በአዋጁ እንደተገለፀውም መታወቂያው ራሱ ቁጥሩ ነው።

የፕላስቲክ መታወቂያ ካርድ ማግኘት ከፈለጉ ግን፣ ጊዜያዊ ስምምነት ከኢትዮጵያ ቴሌኮም እና ከፖስታ ቤት ጋር ተፈጽሞ ስለሆነ፣ ከቅርንጫፎቻቸው በመሄድ አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል።

ምዝገባ ከተካሄደ በኋላ መታወቂያ ይሰጣል፤ ሥርዓቱ ዲጂታል ነው። በአዋጁ እንደተገለፀውም መታወቂያው ራሱ ቁጥሩ ነው።

የፕላስቲክ መታወቂያ ካርድ ማግኘት ከፈለጉ ግን፣ ጊዜያዊ ስምምነት ከኢትዮጵያ ቴሌኮም እና ከፖስታ ቤት ጋር ተፈጽሞ ስለሆነ፣ ከቅርንጫፎቻቸው በመሄድ አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል።

ዎች በራሳቸው ፍላጎት የፈለጉትን ቢፈልጉም፣ ዱጂታል ቅጅ (ኮፒ) በቴሌብርና በፋይዲ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) በመግባት፣ ፋይዲ ቁጥራቸውን በማስገባት ዱጂታል ቅጅውን (ኮፒውን) ማግኘት ይቻላል።

በተጨማሪም በወረቀት የትም ቦታ በማሳተም አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል። ሥርዓቱ አካሊዊ መረጃ ተመስርቶ የሚሰጥ ሲሆን፣ አንዴ ሰው አንዴ መሆኑን የሚያረጋግጥና አንዴ ሰው ሁለት እና ከዚያ በላይ በተለያየ ስም መያዣ አይችልም።

አበመጨረሻ፣ “የፋይዲ ሥርዓት ሰው ተኮር ሆኖ ሰዎችን ከአገልግሎት ጋር በተያያዘ ተጠቃሚ ለማድረግ የተዘጋጀ ነሮግራም ነው። በተለይ አገልግሎትን ለማሳሰብ ከገቢዎች፣ ከመሬት ካርታ እና ፕላን ከገንዘብ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ማጭበርበሮችን ይደቀማል።

በቀጣይ ሰዎች ወደ ተቋማት ሳይሄዱ፣ ከቤታቸው ወይም ባለበት ቦታ ሆነው ሳይንግሊቱ በስሌክ አገልግሎት የሚያገኙበት ሥርዓት ነው። ስለዚህም ሁለም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁን” ይህ መልእክታችን ነው።

ሰላም!

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top