Economic offices

የስራ ዕድል ፈጠራ እና ኢኮኖሚ ክላስተር

  • እንደ ሀገር የድህነት ምጣኔን ለመቀነስና የዛጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የስራ ዕድል ፈጠራ የማይተካ ሚና ያበረክታል። በብዙ አካባቢዎች ወጣቶች የስራ ዕድል አማራጮችን በመጠቀም የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ነው።
  • በዚህም በየአመቱ በሚቆጠሩ ስራ አጦች የስራ ዕድል እየተፈጠሩ ናቸው። ከነዚህ የስራ አጦች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር የተፈለገው ደረጃ ሊይ ተደርጓል። ባለመሆኑም ሀገሪቱ ባለኩት ውስን ሀብት አኳያ አፈጻጸሙ አበረታች እንደሆነ መታወቅ ችሎታ አለው።
  • በዚህ ጽሐፋችን በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ኢኮኖሚ ክሊስተር የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዩኒት የ2017 በጀት አመት የስራ አፈጻጸምን ለማስቃኘት ወደድን። በዓለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ኢኮኖሚ ክሊስተር የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዩኒት በበጀት ዓመቱ የከተማውን ስራ አጦች የስራ ዕድል ባለቤት ለማድረግ የተዘጋጁ ስራዎች መሰራታቸውን ከዩኒቱ ያገኘነው መረጃ የሚያስመልክት ነው።
  • በከተማ አስተዳዳሩ የስራ ዕድል ፈጠራን በክህሎት መር ማድረግ ሀብት ያካበቱ ኢንተርፕራይዝን ለመፍጠር እየተሰራ ያለው ስራ ውጤት እየታየበት ነው። የስራ ዕድል ፈጠራው ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዘ ችግሮችን ለመፍታት አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። በከተማ አስተዳዳሩ የሚገኙ ስራ አጦችን በመለየት እና ወደ ስራ በማስገባት ለብዙ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ይታወቃል። ከማስፈጸም አቅምና ከስራ ፈላጊች አመለካከት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ስለማስተዋል ይታወቃል።
  • በመስጠት ዚጎችን ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የማድረግ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል። የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳዳር ኢኮኖሚ ክለስተር የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ሌማት ዩኒት መሪ አቶ ኑረዲን ሸረፋ በመናገር፣ ወጣቶች በሚሰማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ አመለካከትን ከመቅረጽ ጀምሮ መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ሥራ እየተሰራ እንደሆነ ነው የተናገሩት።
  •  
  • ፍለጎትንና ገበያን ማዕከል ያደረገ ስልጠና ከመስጠት አኳያም ከሳንኩራ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮላጅ ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ይናገራል።
  • ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር የተያያዘ ችግሮችን ለመፍታት በበጀት አመቱ መጀመሪያ በከተማ አስተዳዳሩ የሚገኙ ሥራ አጦችን በመለየት እና ወደ ስራ በማስገባት ሂደት የተቀናጀ ስራ መሰራቱንም ይገልጻል። ዩኒት መሪ አቶ ኑረዲን ሸረፋ የበጀት አመቱን የስራ ክንውን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ በበጀት አመቱ መጀመሪያ የስራ አጦች ልየታ ተደርጓል እና ወደ ስራ መገባት እንደተከናወነ ነው የተናገሩት። በዚህም በከተማ አስተዳዳሩ በአመቱ መጀመሪያ የስራ አጦች ልየታ መደረጉን ገለጹ፣ 2249 ስራ ፈሊጎችን ለመለየት ታቅዶ 2025 በመለየት ከእቅድ በላይ ተከናውኗል ብለዋል።
  • በከተማ አስተዳዳሩ በተፈጠረው የስራ ዕድል በቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል እንደተፈጠሩ አቶ ኑረዲን ሸረፋ ገለጹ፣ በዚህም በአጠቃላይ በከተማ አስተዳዳሩ በቋሚ የስራ ዕድል ለመፍጠር የታቀደው 1522 ሲሆን ክንውኑ 1323 መሆኑን አንስተው፣ ከዚህም የሴቶች ድርሻ 43% እንደሆነ ገለጹ።
  • ከዙህ ውጭ የውጭ ሀገር የስራ ዕድል የተፈጠሩ እንዲሆኑ ገለጹ፡፡ በቋሚ የስራ ዕድል ውስጥ የግብርና ዘርፍ 32%፣ የኢንደስትሪ ዴርሻ 23% እና የአገሌግልት ዘርፍ 45% መሆኑን አስመልክተዋል፡፡
  • ከጊዜያዊ የስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ አቶ ኑረዲን ሸረፋ እንደገለጹት በከተማ አስተዳዳሩ በጊዜያዊ የስራ ዕድል 360 ታቅዶ 385 ጊዜያዊ የስራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ በበጀት አመቱ በከተማ አስተዳዳሩ በቋሚና በጊዜያዊ የስራ ዕድል ለማሳማራት ከታቀደው 1882 መካከል 1708 ወጣቶች በጊዜያዊና በቋሚ ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፡፡
  • ከስምሪት አካባይ የሴቶች ድርሻ 43% ነው፡፡ አፈጻጸሙ ያለፈው አመት ዝግተኛ እንደሆነ አስታውሰዋል፤ በ2017 የበጀት አመት ግን የተሻለ አፈጻጸም እንደተመዘገበ ተገልጿል፡፡
  • በአብዚኛው የስራ ዕድል የተፈጠሩ የስራ ዘርፎች ማኑፋክቸሪንግ፣ የብረታ እና እንጨት ምርቶችን በማምረት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ተሰርቷል፡፡
  • በአገልግሎት በሻይ ቡና፣ በመጠጥ፣ በምግብ ቤቶችና በሌሎች በግብርና ዘርፍ ፍራፍሬ ልማት እና በተለያዩ ሰብር ማምረት የተሰማሩ ሰፊውን የስራ ዘርፎች ይወስዳሉ፡፡
  • የበጀት አመቱን የዩኒት የስራ ክንውን አስመልክተው አቶ ኑረዲን የገለጹት የብድር ስርጭትና አመልካሽ ነው፡፡ በአመቱ መጀመሪያ በማህበር ተደራጅተው ወደ ስራ ለሚገቡት ቁጥባ ቀዳሚ ይሰጣል፡፡ ግባር እንደሆነ አንስተው በአመቱ ወደ ስራ የሚገቡ ስራ ፈሊጎች 32,093 ብር ለመስቆጠብ ታቅድ 172,000 ብር በማስቆጠብ መቶ ከመቶ በላይ የሆነ አፈጻጸም ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
  •  
  • ከቁጥባ ጎን ለጎን የሚከናወነው ብድር ለማስመላለስ እንደሆነ አንስተው በዙም 5,424,574 ብር ለማስመላለስ ታቅድ 4,321,996 ብር ተሰራ፡፡ ከተመለሰው ውስጥ _____ ብር በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከደቡብ ካፒታል ሉዝ ማሽን ዕዳ የተመለሰ ሲሆን ቀሪው በኦሞ ባንክና በሌሎች የብድር ማይክሮ ፋይናንሶች የተሰራጨና የተመለሰ 445,470,248 ብር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከዙህ ጋር የአፈጻጸም ጉዳት ሆኖ የታየው በየደረጃው ያለው የብድር አስመልክት ግብረ ሃይል በየጊዜው ሂደቱን እየገመገመና የቀጣይ አቅጣጫ እያስቀመጠ ያለ መሄድ ችግር የታየ መሆኑን አስመልክተዋል፡፡ የብድር ስርጭት ወደ ስራ ለሚሰማሩት መነሻ ካፒታሌ በመሆኑ በበጀት አመቱ በከተማ አስተዳዳሩ 3,826,320 ብር ብድር ለማሰራጨት ታቅድ 3,870,000 ብር ተሰራጭቷል፡፡
  •  
  • በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የማምረቻና መሸጫ ሸድችን ከማመቻቸት አንጻር ጥሩ ውጤት የተገኘ እንደሆነ የገለጹት አቶ ኑረዲን ፣ የስራ ዕድል ፈጠራው የዛጎችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ በከተማ ሁለንተናዊ ብልጽግና እንደረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዲሇውም አስመልክተዋል፡፡ከሸድ ግንባታ ጋር በተያያዘ በአመቱ 1 ሄ/ር መሬት ሸድችን ለመገንባት ለማስተላለፍ ታቅድ ተዘጋጅቷል፡፡1.468 ሄ/ር መሬት ማስተላለፍ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ ሼድችን ለማስመላለስ ታቅድ 07 ሼድችን ማስመላለስ ተችሏል፡፡ በአጠቃሊይ በበጀት አመቱ ከሼድ አቅርቦት ጋር በተያያዘ የተገነቡ እና የተመለሱትን ጨምሮ 06 ታቅድ 07 ሼድችን ማዘጋጀት ተችሏል፡፡
  •  
  • የስራ ዕድል ለተፈጠሩት ወጣቶች የሀገር ውስጥ የገበያ ትስስር እና በውጭ ሀገር የገበያ ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፣ በተለይ በሀገር ውስጥ ዴጋፍ 2,024,347 ብር የገበያ ትስስር ለመፍጠር ታቅዶ 2,159,050 ብር ተደርጓል፡፡ የደረጃ ሽግግርን በተመለከተም ሞዳል የሆኑትን መምረጥ እና ማሸጋገር አስፈላጊ በመሆኑ 09 ለማሸጋገር ታቅድ 08 ማሸጋገር ተችሏል፡፡የሞዴል መረጣ እና ተሞክሮ ቅመራን በተመለከተ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክተው በሰጡት ገለጻ ሞዴል መረጣ 06 ታቅድ 04 ፣ እንዲሁም ተሞክሮ ቅመራ 06 ታቅድ 05 መከናወኑን ገለጸዋል፡፡
  •  
  • ከአንዴ ማዕከል ጋር በተያያዘ ሞዴል ማዕከልን ከመፍጠር አኳያ 01 አንድ ማዕከልን ለማጠናከር ታቅድ 01 ተከናውኗል፡፡አፈጻጸሙም መቶ 17  ከመቶ በላይ ነው ብሎ ይገልጻል፡፡
  • በበጀት አመቱ ያጋጡት ችግሮችን በተመለከተ አቶ ኑረዲን እንዲሉት፣ ከኦሞ ባንክ ጋር በተያያዘ የብድር አቅርቦት ችግር በዋናነት የሚጠቀሰው እንደሆነ አንስተው ገለጸዋል፡፡ በተለይ ከ50,000 ብር በላይ ብድር ለሚወሰዱ ኢንተርፕራይዝ ወደ ዞን ጸድቆ ከተለከ በኋላ የአሰራር መሻጥ ጊዜ ችግር እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይ የጥሬ ገንዘብ እጥረት፣ በግብርና ዘርፍ ለሚሰማሩትም የግብአት አቅርቦት ችግር እና በቂ መሬት ያለማግኘት ችግር ስራ አጦችን ወደ ስራ በማስገባት ሂደት ተግዳሮቶች እንደነበሩ ተገልጿል፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ክትትልና ዴጋፍ በማድረግ፣ በስልክና በአካል በመገኘት የመደገፍ ስራ ተሰርቷል፡፡ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ጋር ተቀራርቦ በመስራት ችግሮችን የመፍታት ስራ እንደሚከናወን ገለጸዋል፡፡
  • በከተማ አስተዳዳሩ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ደረጃም ለጉዳዮች ያልተቋረጠ ክትትል በማድረግ ዘርፎችን ክትትል በማድረግና በየጊዜው እየገመገመ የሚስተዋለ ችግሮችን በማረም የሰሩት ስራም በበጀት አመቱ ለአፈጻጸሙ ማደግ እንደቻሉ ገለጸዋል፡፡

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top