604823431_1175192538125956_5389917250855955884_n
እንኳን ወደ ዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር በደህና መጡ
previous arrow
next arrow

የዓለም ገበያ ከተማ ከንቲባ መልክት

 

የዓለም ገበያ ከተማ የከተማ አስተዳደር መዋቅር ዕዉቅና አግኝታ ወደ ስራ ከተገባ ከአራት ዓመታት የማይዘል ግዜ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በነዚህ አጭር ዓመታት ዉስጥ የመንግስት ተቃማትን በአዲስ መልኩ ከማደራጀት ጎን ለጎን የከተማችንን ህብረተሰብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፤ አሁንም በመሰራት ላይ ናቸዉ፡፡ የአንድን ከተማ ዕድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ግልፅ፤ ቀልጣፋና ፍትሃዊ የመንግስት አገልግሎት እንዲሁም ለከተማዉ ማህበረሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን መዘርጋትና መገንባት ወሳኝ ጉዳዮች ናቸዉ፡፡
በመሆኑም የከተማችንን ዕድገት ለማፋጠን፤ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ፤ ለነዋሪዎቿ ምቹና ተስማሚ ለማድረግ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን የከተማችንን ህዝብ በማሳተፍ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚረዱ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

በዚህም በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት በከተማችን የመሬት መረጃ አያያዝ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የአይ ሲቲ መሰረተ ልማት ዝርጋታ በማካሄድ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓታችንን የማዘመን ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
የከተማችንን የዉስጥ ለዉስጥ የመንገድ ችግር ለመፍታት አዳዲስ መንገዶችን የመክፈት፤ነባር መንገዶችን የመጠገን፤ዋና ዋና መንገዶችን ጌጠኛ ድንጋይ የማልበስ፤የመንገድ አካፋዮችን የማልማትና ሌሎችም የመንገድ ልማት ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
በተጨማሪም ከመንግስትና ከከተማችን ህብረተሰብ በተገኘ ድጋፍ የከተማችን ህዝብ የረጅም ግዜ ጥያቄ የነበሩ የማህበረሰብ ፋርማሲ እንዲሁም የዶሎሎ ወንዝ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 ድልድዮችን በአጭር ግዜ በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል፡፡
በከተማችን የገጠር ቀበሌያትም የተለያዩ የግብርና ኢኒሽዬቲቮች ላይ አ/አደሩን በማሳተፍ የተለያዩ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በገጠር የአ/አደሩን የአኗኗር ዘይቤ የሚቀይሩ የግብርና ጎዳናዎችን በመፍጠር ለገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ምቹ መደላድል መፍጠር ተችሏል፡፡
በከተማና ገጠር ኮሪደር ልማት ስራ በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት ያሉንን ፀጋዎች በመለየቴ የተጀመረዉ እንቅስቃሴ በ 2018 ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
እነኚህና ሌሎች ያልተጠቀሱ ተግባራት ከተማችን ለማደግና ለመበልፀግ ምቹ ሁኔታ ያላት መሆኑን የሚያሳየን በመሆኑ መላዉ የከተማችን ማህበረሰብ ከከተማዉ መንግስት ጎን በመሆን የተለመደ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡

ተልዕኮ

ሁለንተናዊነትን ያማከለ እና የሀገር ግንባታ መሰረት ያደረገ ውጤት ማስመዝገብ ።

ዓላማ

ወጪ ቆጣቢ፣ ቀልጣፋና ፍተሃዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስርዓት በማሰፈን ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ነው።

እሴት

አገልጋይነት ፤ ታታሪነት ፣ ምስጉንነት፣ ስራ ወዳድነት ፣ ውጤታማነት ፣ በቲም መንፈስ መስራት ፣ ታማኝነት

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top