የበርበሬ ምርትን የግብይት ማዕከላት በማዘመንና የገበያ ትስስሩን በማጠናከር የአምራቹን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ጥራቱን የጠበቀ የበርበሬ ምርት ለሀገር ዉስጥና ለዉጭ ሀገር ገበያ ለማቅረብ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቆመ!

ዓ/ገበያ፣ የካቲት 07/2018 (ዓገከመኮ)
በስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ የቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተዉፊቅ ኑሪ በዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የበርበሬ ግብይትን ተዘዋዉረዉ ተመልክተዋል።
የስልጤ በርበሬን ከሀገር ውስጥ ፍጆታ በተጨማሪ ወደ ማዕከላዊ ገበያ በስፋት እየቀረበ እንደሆነ እና ከሀገር ውጭም ኤክስፖርት እየተደረገ መሆኑን ያነሱት አቶ ተዉፊቅ ለዚህም ግብይቱ ደረጃዉን በጠበቀና በዘመነ የግብይት ማዕከል ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።
የበርበሬ ምርትን የግብይት ማዕከላት በማዘመንና የገበያ ትስስሩን በማጠናከር የአምራቹን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ጥራቱን የጠበቀ የበርበሬ ምርት ለሀገር ዉስጥና ለዉጭ ሀገር ገበያ ለማቅረብ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባዉም አቶ ተዉፊቅ ጠቁመዋል።
የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ናስር አህመድ በበኩላቸዉ በከተማዉ በስፋት እየቀረበ ያለዉን የበርበሬ ምርት ግብይት በአንድ ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል የግብይት ማዕከል ለመገንባት እንደታቀደና በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌሰቡክ➲https://www.facebook.com/100069056625352/
ዩቲዩብ➲https:http://youtube.com/@alemgebeyacommunication-f7l…
ቴሌግራም➲https://t.me/alemgebeyacommunicationoffice
ቲክቶክ➲tiktok.com/@alemgebeyacommunication0
ኤክስ X➲https://x.com/alemgebeyacommu/status/1803607427415232695?t=6Ar4b99EJ3yLzGds4RQhDA&s=
ኢንስታግራም ➲https://www.instagram.com/alemgebeyacommnication/profilecard/?igsh=MWp6OGR6YWN2Z3VidQ==

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top