የዓለም ገበያ ከተማ ከንቲባ መልክት
የዓለም ገበያ ከተማ የከተማ አስተዳደር መዋቅር ዕዉቅና አግኝታ ወደ ስራ ከተገባ ከአራት ዓመታት የማይዘል ግዜ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በነዚህ አጭር ዓመታት ዉስጥ የመንግስት ተቃማትን በአዲስ መልኩ ከማደራጀት ጎን ለጎን የከተማችንን ህብረተሰብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፤ አሁንም በመሰራት ላይ ናቸዉ፡፡
Read More
የአንድን ከተማ ዕድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ግልፅ፤ ቀልጣፋና ፍትሃዊ የመንግስት አገልግሎት እንዲሁም ለከተማዉ ማህበረሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን መዘርጋትና መገንባት ወሳኝ ጉዳዮች ናቸዉ፡፡
በመሆኑም የከተማችንን ዕድገት ለማፋጠን፤ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ፤ ለነዋሪዎቿ ምቹና ተስማሚ ለማድረግ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን የከተማችንን ህዝብ በማሳተፍ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚረዱ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
በዚህም በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት በከተማችን የመሬት መረጃ አያያዝ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የአይ ሲቲ መሰረተ ልማት ዝርጋታ በማካሄድ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓታችንን የማዘመን ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
የከተማችንን የዉስጥ ለዉስጥ የመንገድ ችግር ለመፍታት አዳዲስ መንገዶችን የመክፈት፤ነባር መንገዶችን የመጠገን፤ዋና ዋና መንገዶችን ጌጠኛ ድንጋይ የማልበስ፤የመንገድ አካፋዮችን የማልማትና ሌሎችም የመንገድ ልማት ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
በተጨማሪም ከመንግስትና ከከተማችን ህብረተሰብ በተገኘ ድጋፍ የከተማችን ህዝብ የረጅም ግዜ ጥያቄ የነበሩ የማህበረሰብ ፋርማሲ እንዲሁም የዶሎሎ ወንዝ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 ድልድዮችን በአጭር ግዜ በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል፡፡
በከተማችን የገጠር ቀበሌያትም የተለያዩ የግብርና ኢኒሽዬቲቮች ላይ አ/አደሩን በማሳተፍ የተለያዩ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በገጠር የአ/አደሩን የአኗኗር ዘይቤ የሚቀይሩ የግብርና ጎዳናዎችን በመፍጠር ለገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ምቹ መደላድል መፍጠር ተችሏል፡፡
በከተማና ገጠር ኮሪደር ልማት ስራ በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት ያሉንን ፀጋዎች በመለየቴ የተጀመረዉ እንቅስቃሴ በ 2018 ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
እነኚህና ሌሎች ያልተጠቀሱ ተግባራት ከተማችን ለማደግና ለመበልፀግ ምቹ ሁኔታ ያላት መሆኑን የሚያሳየን በመሆኑ መላዉ የከተማችን ማህበረሰብ ከከተማዉ መንግስት ጎን በመሆን የተለመደ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት ሰው ተኮር የሆኑ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎችና ፕሮግራሞችን በመቅረፅ የህብረተሰባችንን ኑሮ በሁሉንተናዊ መልኩ የሚያሻሽሉና የሚደግፉ ተግባራትን በጊዜ የለኝም መንፈስ በመከወን ለይ ይገኛል።
የህብረተሰብ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ሁሉንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ እየተጋለ የሚገኘው ፓርቲያችን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ፍትሃዊና ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት 7/24 እየሰራ ይገኛል።ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በጥራት፣ በፍጥነት፣ በትጋትና በብቃት ጀምሮ መጨረስ የብልፅግና ፓርቲ መገለጫ ነው።
ለዚሁም አንደ ማሳያ የሚሆነው በከተማችን ዓለም ገበያ በስፋት እየተከናወኑ የሚገኙ የአንድ ከተማ ፕሮጀክት ኢኒሽዬቲቭ አካል የሆኑ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎችና ሌሎች የልማት ስራዎች አፈጻጸም ነው።
Read More
በከተማችን ለውጥ ውስጥ ትልቅ ድርሻ የያዘውን ፕሮጀክት በተለየ ሁኔታ በጥበብ ጀምሮ በተቀመጠው ጊዜ በጥራት የማጠናቀቅ ድንቅ ባህልን መገንባት ተችሏል።እስካሁን የተገኘውን ልምድ ወደ ባህልነት ደረጃ በማሳያ ጀምሮ መጨረስ የመንግስት መለያ ከሆነ ሰነባብቷል።ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመዘገበ የሚገኘው የትብብር የመቻል የተለወጠ ነፃብራቅ በፕሮጀክቶች ውስጥ እየሆነ ይገኛል። ሀገራችንን ብሎም ከተማችንን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሳደግ በትጋት እየተከናወነ በሚገኘው ድንቅ ጉዞ ውስጥ የመቻል ለውጥ በማጎናፀፍ ለይ የሚገኘው የብልጽግና ፕሮጀክት ጀምሮ የመጨረስ ውጤታማ የባህል ለውጥ እምርታ ነው።ከተማችንን የማዛመንና የማስዋብ ለህብረተሰቡ አመቺ ማድረግ የመንግስታችንና የፓርቲያችን የፖሊሲ ፕሮግራም ውጤቶች ናቸው።
በዚህም የህብረተሰቡ ተሳትፎ የማይተካ ሚና ነበረው፤ በተለይ የከተማችን ባለሀብቶች፣ የንግድ ማህበረሰብ፣ ወጣቶችና ሴቶች ከተማችንን ለማዛመን በሚደረገው እንቅስቃሴ ለይ የነበራቸው ድርሻ የጎላ ነው። የዓለም ገበያ ከተማ ማህበረሰብ "የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት" ስራ እንዲሳካ ቀን ተሌት በመሳተፍ የስራው ባለቤት ሆኖ ለደረገው የነበረ እንቅስቃሴን እንዲሁም የከተማ አመራሩ በሙሉ አቅሙ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን እንዲሰሩ ላበረከተው የጎለ አስተዋጽኦ ያለኝን ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና አቀርባለሁ። በከተማው እየተሰራ ያለው የልማት ስራ በከተማ አስተዳደሩ እስከአሁን እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን በጉልህ የሚያሳድግ በመሆኑ ህዝቡ እስከአሁን እየተሰጠ ያለውን አዎንታዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክቴን አስተላልፈለሁ።
በ ሀገራችን ብሎም በከተማችን ድህነትን ማስወገድ ዋነኛው የልማት አጀንዳ ሲሆን ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ከለዉጡ ወዲህ ባሉ ዓመታት የሚጠበቁ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል፡፡
በዚህም አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህ እየተመዘገቡ ያለ ሁለንተናዊ የልማት ውጤቶች በመንግስትና በህዝብ የተቀናጀ ጥረት በመሆኑ ይህንን ጥረት ወደ ለቀ ደረጃ ለማሸጋገር በየበጀት ዓመቱ ያለ መልካም ውጤቶችን ይበልጥ ለማስፋፋትና መሰረት ለማስያዝ እንዲሁም እጥረቶችን በመቅረፍና ወደ ታለመለት ግብ በመድረስ የተያዘውን የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ ሰፋፊ ስራዎች በመከናወን ለይ ናቸው።
በአካባቢው የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን እና ወቅታዊ መረጃዎችን የተለያዩ የሚድያ አማራጮችን በመጠቀም ለአካባቢው ህብረተሰብ በማቅረብ የሚዲያ አሰራሮችን ብቃትና የአካባቢውን ህብረተሰብ ግንዛቤ ማጎልበት ይጠይቃል፡፡ በአስተዳደራዊ ክሊስተር ስር ከተደራጁ ተቋማት መካከል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ክፍሌ አንደ መሆኑ ይታወቃል።
Read More
በከተማ አስተዳደራችን ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ዋና ዋናዎችን በመምረጥ በህትመት ሚዲያ ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ከሚደረግባቸዉ መንገዶች አንዱ ደግሞ መፅሔት በማዘጋጀት የማሰራጨት ስራ መስራት ነዉ፡፡ በመሆኑም ባሳለፍነዉ በጀት ዓመት ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የተመረጡ ተግባራትን በፅሑፍ በማዘጋጀት እነሆ ኡሎ የተሰኘች የዉስጥ መፅሔትን ጀባ ብለናችኋል፡፡ መልካም ንባብ
ኡሎ፡- የዓለም ገበያ ከተማ በከተማ አስተዳደርነት ከተዋቀረች ወዲህ ባሉ ዓመታት በከተማ መሬት ልማት ፕለን ዝግጅትና መሬት ነክ ስራዎች ጋር በተያያዛ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በአጭሩ ቢገልጹልን?
አቶ ሱልጣን፡- እንደ ከተማችን ከተማችን በከተማ አስተዳደርነት እውቅና አግኝታ ወደ ተግባር ከገበንበት ጊዜ ጀምሮ በከተማው ማዘጋጃ ቤት በመሬት መሬት ነክ እንዲሁም ፕለን ትግበራ በርካታ ተግባራት ተከናውኗል፡፡
ከመሬት ዝግጅት አንፃር መሬትን ለተለያዩ ከመዘጋጀት አንጻር እንደ ከተማችን ለንግድና ኢንቨስትመንት ለቤቶች ህብረት ስራ ማህበራት /በአናስተኛ የኑሮ ደረጀ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፊሎች የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በከተማችን 163.7 ሄ/ር መሬት በማዘጋጀት ልዩልዩ ፍላጎቶችን ለማሟለት ጥረት ተደርጓል፡፡
Read More
ከዚህም ውስጥ ለንግድና ኢንቨስትመንት 22.5 ሄ/ር መሬት በማዘጋጀት፡ ለኢንደስትሪ ልማት የሚውል 15.5 ሄ/ር አዘጋጅቶ በማቅረብ ለከተማ ግብርና / ለወተት እርባታ ኢንቨስትመንት 13.5 ሄ/ር፡ ለአልግሎት ሰጪ ተቋማትና ለማህበራዊ ግልጋሎት ለሚሰጡ ተቋማት 56.2 ሄ/ር መሬት እንዲሁም ለጥቃቅን አነስተኛ ማምረቻና መሸጫ 8.6 ሄ/ር በድምሩ 163.6 ሄ/ር ለሚፈለገው አገለግሎት በማቅረብ የከተማችንን እድገትና የማህበረሰቡን ፍላጎት ለመመለስ ጥረት ተደርጓል፡፡
ኡሎ፡- ከከተማ ቤቶች ልማትና የጽደት አስተደዳር ስራዎች አንጻርስ ምን ምን ተግባራት ተከናወኑ?
አቶ ሱልጣን፡- የከተማችን የፅድት አስተደዳር ስራን በተመለከተ እንድ የከተማችንን ውበት ለመጠበቅ በርካታ ተግባራትን እየተከናወኑ ስሆን የብሎክና የመንደር አደረጃጀትን አጠናክሮ በማስኬድ የከተማው የፅደት ስራ ዘለቂ እንዲሆን ተሰርቷል በዚህም የተሸለ ለውጥ ማምጣት ተችሎል ከዝህ ተግባር አንፃር በተጨማሪ ሳምንታዊ የፅደት ዘመቻን ባህል እንዲሆን ሰፊ ስራ ተሰርቷል ሌለው እንደ ከተማችን ከ 9 የፅደት ማህበራትን እንደ ከተማ አደራጅተን በ6 መንደሮች የተሟለ የጽደት ዕቃ በሟሟለት የዘወትር ስራ እንዲሆን እየተሰረ ይገኛሌ ፡፡ እንዱሁም በከተማችን ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ በበጀት በማስቆፈር ለአገልግሎት ምቹ ማድረግ ተችሉል፡፡
ኡሎ፡- የከተማዉ የመሰረተ ልማት ስራዎች አፈፃፀምስ ምን ይመስለል?
አቶ ሱልጣን፡- የከተማችንን የመሰረተ ተግባራትን በተመለከተ አለም ገበያ ከተማ ለኑሮ ተስማሚና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ በእቅድ ተይዞ የፕለን ማስጠበቅ ስራዎችን በከተማው በስፋት የተሰራበት ዘርፍ ነው ይህም ሲባል እንደ ከተማ ፕለንን ጠብቀው ያልተከፈቱ የፕለን መንገደችን የመክፈት ስራ ተሰርቷል በዚህም 125 ኪ/ሜ መንገድ የመክፈትና የከተማውን የዕድገት ደረጀ በሚመጥን ሌክ ማስጠበቅ ተችለል፡፡
እንዲሁም የጠጠር መንገድ ጥገና 185 ኪ/ሜ በመስራት የከተማውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችለል፡፡ ሌላው በተለይም ከተማ አስተዳደር ከሆንን ወዲህ እንደ ከተማ ከተማችንን በመሰረተ ልማት በማስተሳሰር ከከተማችን ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት በመስራት የውስጥ ለውስጥ መንገድችን በጌጠኛ ድንጋይ ወይም ኮብሌስቶን በመስራት የከተማችንን ውበትና የመሰረተ ልማት ተደራሽነትን ችግር ለመቅረፍ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል በዙህም እንደ አለምገበያ ከተማ 25.5 ኪ/ሜ የኮብሎስቶን መንገድ ስራ ተግባራዊ ማድረግ ተችለል፡፡ በሌላ በኩል ከከተማ መሰረተ ልማት ውስጥ አንደ እና የከተማዉ ማህበረሰብ የዘወትር የመሰረተ ልማት ጥያቄ የሆነው የመንገድ ውሃ መውረጃ ቦይ / ዲች ግንባታ ነው. ከዚህ ተግባር አንጻር እንደ ከተማችን በከተማው አስፈለጊ ቦታዎችን ልየታ በማድረግ በከተማው ማህበረሰብ እና በመንግስት ተሳትፎ በከተማው 6 መንደሮች ውስጥ 45.5 ኪ/ሜ ዲች ግንባታ በመፈጸም የህብረተሰቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄ መመለስና ተደራሽ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል፡፡ በተጨማሪ እንድ ከተማችን ቀበሌን ከቀበሌ የሚያገናኙ መንገዶችን ከመስራት አንፃር በከተማ ውስጥ ለውስጥ በቦሮቦርና አፈር በፈር 318 ኪ/ሜ መንገድ ተሰርቷል፡፡
Read More
ሌላኛው ከከተማ ጽደትና ውበት ስራ አንደ የሆነው የግሪነሪ ስራ ነው ከዚህ ዘርፍ እንደ ከተማችን በከተማችን በፕሊን የተመላከቱ 03 አካፋይ መንገዶችን ለማልማት ታቅዶ በድምሩ 5 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው አካፋይ መንገድ በማልማት ከተማችንን ውብና ነፋሻማ ከማድርግ ባለፈ ከተማችን እየተከተለች ላላው የስማርት ሲቲ ምዕራፍ ግንባታ አስተወፅኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ እንደ ከተማችን መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄ የሆነው ከተማውን ለሁለት የሚከፍለው የደሎሎ ወንዝ ድልድይ ግንባታ እንደነበር ግልጽ እንደመሆኑ በከተማችን ደረጀ 03 በአስፈለጊ ቦታ ድልድይ ግንባታ ለማከናወን ታቅዶ በህ/ሰብ ተሳትፎና በመንግስት ትብብር በአጭር ጊዛ 02 ድልድዮችን ግንባታቸውን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት በማብቃት የህ/ሰቡን የረዥም ጊዛ ጥያቄ መመለስ የተቻለበት ነዉ፡፡
ኡሎ፡- በአጠቃሊይ በማዘጋጃ ቤቱ የመረጃ አያያዜን ለማዘመን የተሰሩ ስራዎችና ዉጤታቸዉስ?
ኡሎ፡- በአጠቃሊይ በማዘጋጃ ቤቱ የመረጃ አያያዝን ለማዘመን የተሰሩ ስራዎችና በዚህም የመረጃ አያያዝ ስርዓታችንን ካዘመንን ዉጤታቸዉስ?
አቶ ሱሌጣን፡- የማዘጋጀ ቤቱን የመሬት መረጀ አያያዝ የማዘመን ስራን በተመለከተ እንደ ከተማችን ከዚህ በፊት በተቋሙ አገልግሎት ለመስጠት የማይመችና የባለጉዲይ መጉላላት በስፋት ይስተዋል የነበረበት በመሆኑ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በከተማ ደረጃ በመወያያት ያለውን የመረጃ ስርዓት ችግር በምን መልኩ መፍታትና እንዴትስ ቢሰራ የመረጀ ችግሩን መፍታትና የባለጉዯይ እንግልትና እሮሮ መመለስ እንዲለብን ተወያይተን በመግባት ፤ የመሬት መረጃን አያያዝ ስርዓታችንን በማዘመን ዱጂታሊይዝ ማድረግ ተችልል።የማዘጋጃ ቤቱን የቢሮ አደረጃጀቱንም በማስተካከል ለአገልግሎት ምቹ እንዲሆን በማድረግና አጠቃለይ በተቋሙ የሚገኘውን የመሬት መረጀ ከ7000 ፋይሎች በለይ ወደ ሶፍት በማስገባት በዘመናዊ መልኩ እዲደራጁ ማድረግ ተችለል፡፡
በኋላ እንደ ተቋም የመጣ ለውጥን በሚመለከት ከዚህ ቀደም የአንድ ባላይዞታ ፈልጎ ለማግኘት አስቸጋሪ የነበረውን የመረጀ ችግር መቅረፍ ተችላል የባለጉዳይ እንግልትን ማስቀረትና አገልግሎትን ቀልጣፋና ጊዜና ወጪ ቆጣቢ በመደረግ ከምልልስ የጸዳ ስራ ለመስራት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
