በከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ማህበራዊ መሰረቶች የብልፅግና ፓርቲ የአባላት ኮንፈረንስ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ!

ዓ/ገበያ፣ የካቲት 5/2018 (ዓገከመኮ)
በስልጤ ዞን ዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር “ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር!”በሚል መሪ ቃል በከተማዉ እና በገጠር ቀበሌያት ባሉ ሁሉም የብልፅግና ፓርቲ ህብረት የአባላት ኮንፈረንስ እና የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ ተካሂዷል።
ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት ኢኮኖሚያዊ ሽግግር መረጋገጡና ፖለቲካዊ እንዲሁም ማህበራዊ ማንሰራራት መጀመሩ በመድረኩ ተነስቷል።
በመድረኩ ላይ ምርጫ በፖለቲካ ሂደት ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ ተገልጾ፤7ኛው ሀገራዊና አካባቢያዊ ምርጫ ፓርቲው ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር የሚጠቀምበት መድረክ መሆኑ ተመላክቷል።
የብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚጠቀምበት ምልክት“የስንዴ ነዶ“መሆኑ በይፋ ተገልጿል።
በኮንፈረንሱ የፓርቲውን አሰራር በማጠናከርና ክፍተቶችን በመለየት፣በመጪው ምርጫ ውጤታማ ለመሆን ያለመ ነው።
ተሳታፊ አባላቱም የቀረቡትን አቅጣጫዎች ወደ ተግባር በመለወጥ ለሀገር ግንባታ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ እና የብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን ኮሚሽን የ6ት ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ፀድቋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌሰቡክ➲https://www.facebook.com/100069056625352/
ዩቲዩብ➲https:http://youtube.com/@alemgebeyacommunication-f7l…
ቴሌግራም➲https://t.me/alemgebeyacommunicationoffice
ቲክቶክ➲tiktok.com/@alemgebeyacommunication0
ኤክስ X➲https://x.com/alemgebeyacommu/status/1803607427415232695?t=6Ar4b99EJ3yLzGds4RQhDA&s=
ኢንስታግራም ➲https://www.instagram.com/alemgebeyacommnication/profilecard/?igsh=MWp6OGR6YWN2Z3VidQ==

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top