በከተማ አስተዳደሩ ወቅታዊና መደበኛ ተግባራት የእስካሁኑ አፈፃፀም ተገመገመ።By alem / November 25, 2025 ሕዳር፣14/2018(የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን )በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ወቅታዊና መደበኛ ተግባራት የእስካሁኑ አፈፃፀም ተገምግሟል።የወቅታዊና መደበኛ ተግባራት የአፈፃፀም ሪፖርት በዋናነት የመከላከያ ምልመላ፣የስራ ዕድል ፈጠራ፣የግብርና ተግባራት፣የንግድ፣የገቢ አሰባሰብ ከሚመለከታቸው የተቋም ኃላፊዎች በዝርዝር ቀርቧል።መድረኩን የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ዩኒት አቶ ሐምዱ ሸሚል እና የከተማ አስተዳደሩ የግብር ዩኒት አቶ ኑርታታ ሙንዲኖ መርተውታል።በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርት መነሻ የመድረኩ ተሳታፊዎች በጥንካሬና በጉድለቶች ዙሪያ ሐሳብ አስተያየት አንስተው ጥንካሬዎች ለማስቀጠል እና በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ውስንነቶች ፈጥኖ ለማረም መግባባት ተፈጥሮባቸው መድረኩ ተጠናቋል።