የክልሉ መንግሰት ያሰቀመጣቸው አቅጣጫዎችና አዳዲሰ ኢንሼቲቮችን በመተግበር ረገድ እምረታዊ ለውጦች ማስመዝገብ ተችሏል – አቶ ዘሪሁን እሸቱBy alem / November 25, 2025 ህዳር፣13/2018(ዓለም ገበያ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ በክልሉ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣጡ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት ዘንድሮ የሚከበረው 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ከሌሎች ወቅቶች የሚለየው በሀገር ደረጃ ትላልቅና ሜጋ ፕሮጀክቶች የተጠናቀቁበት እና አዳዲስ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ደግሞ የተጀመረበት በመሆኑ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች እንደምትችል ማረጋገጥ የተቻለበትን እድል መፈጠሩን የገለጹት ኃላፊው ክልሉ እንደ አዲሰ በተመሰረበት ማግስት መሆኑ ከሌሎች በዓላት ልዩ ያደርገዋል ሲሉም ኃላፊው አብራርተዋል።የክልሉ መንግሰት ያሰቀመጣቸው አቅጣጫዎችና አዳዲሰ ኢንሼቲቮችን በመተግበር ረገድ እምረታዊ ለውጦችን አሰመዝግቦዋል ሲሉም አቶ ዘሪሁን በመግለጫቸው አብራርተዋል።ክልሉ ሲመሰረት በልዩ ልዩ ጫናዎች ውስጥ በማለፍ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ዘሪሁን በተለይ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ማጋጠሙን ጠቁመዋል።ይህን ተከትሎም በአንዳንድ ተቋማት የመንግስት ሰራተኞችን ደመወዝ መክፈል ያልተቻለበት እንዲሁም ከፍተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የተስተዋለበት ወቅት እንደነበርም ኃላፊው አመላክተዋል።አመራሩም ሆነ ባለሙያው ቀድሞ ከነበረበት ክልል ሲዘዋወር በመንግስታዊ ስራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም አቶ ዘሪሁን በመግለጫቸው አብራርተዋል።ካጋጠሙ ችግሮች ባለፈ መልካም አጋጣሚዎች መኖራቸውንም ኃላፊው አብራርተዋል።የክልሉ ህዝብ የሰራ ፈጠራ ባህሉ የዳበረ መሆኑ እንዲሁምመንግሰት በሚጠይቃቸው የልማት ሰራዎች ተሳታፊ መሆኑንም አቶ ዘሪሁን ጠቁመዋል።ክልሉ ከአዲሰ አበባ በቅርብ ርቀት መገኘቱ እንዲሁም በአመራር ውሰጥ ያለው የለውጥ ፈላጊነትና ተነሻነት መኖሩን በመልካም አጋጣሚነቱ ጠቅሰዋል።ያጋጠሙ ችግሮችን የተረዳው የክልሉ ከፍተኛ አመራር በችግሩ ላይ ከተማመነ በኃላ የአጭር ፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ በማውጣት ውይይት መደረጉን አቶ ዘሪሁን አስታውሰዋል።የክልሉ መንግስት ከህብረተሰቡ ጋር በመምከር የጋራ ተግባቦት መፍጠር መቻሉን ኃላፊው በመግለጫቸው ጠቁመዋል።የክልሉ መንግስት ለሰላም በሰጠው ልዩ ትኩረት 24 ሰዓት ተንቀሳቅሶ መስራት የሚቻልበትን እድል ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት የላቀ ውጤት ስለመመዝገቡም አመላክተዋል።በክልሉ በሁለም መሰኮች ላይ ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት ስኬታማ እንደነበር ያስታወሱት ኃላፊው ትላልቅ ነገሮችን እናሰብ ያሰብነውን ለመፈፀም በፍጥነት እንጀምር በሚል እሳቤ የተከናወኑ ተግባራትን በአብነት ጠቅሰዋል።20ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ የጋዜጠኞች ቡድን አባላት ሰሞኑን በክልሉ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች ላይ ሲያካሔዱት የነበረውን የመስክ ምልከታ አጠናቀዋል። ዘገባው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።