የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የእንኳን ደስ አላችሁና የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ!

ዓ/ገበያ፣ ህዳር 12/2018(ዓገከመኮ)
የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ረሻድ ሀሰን የዓለም ገበያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህዝቡ የረዥም ጊዜ ጥያቄ የነበረውን የኤክስሬይ ማሽን ማስገባቱን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁና የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከአስር ዓመታት በፊት የተመሰረተውና ከተማ አስተዳደሩን ጨምሮ ለሳንኩራ ወረዳና አጎራባች አከባቢዎች ከ1 መቶ 80 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ግልጋሎት የሚሰጠው ሆስፒታል የኤክስሬይ ማሽን በማስገባቱ ለህብረተሰባችን ትልቅ እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ረሻድ ጥያቄያችሁ ፍሬ በማፍራቱ መላዉን ማህበረሰባችንን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።
በተለያዩ አካላት ስናቀርብ ለነበረዉ ጥያቄ ድጋፋቸዉን ሲያደርጉልን ለነበሩ የመንግስት አካላትና ግለሰቦች ላደረጉልን ትብብር ከፍ ያለ አድናቆትና ምስጋና እንዳላቸዉም አቶ ረሻድ ገልፀዋል።
በተለይም የዞን ባለድርሻ ተቋማት፣ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጤና ቢሮ፣ የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ከዞን እስከ ፌዴራል ያሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወካዮቻችንን እንዲሁም ሌሎች ያገባናል ብላችሁ ጥያቄያችንን ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል ስታቀርቡ ለነበራችሁ ሁሉ በከተማ አስተዳደሩና በህዝቡ ስም ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉ ከንቲባዉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top